top of page

ከዚህ ይጫኑ

መግቢያ

 

ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት ብንጀምርስ ብለን ተነሳን፤

የካህኑ ሶዶቅን ምክር አስታከን።

ትዝታና ታሪክ ወደ ኋላ ባይመልስም ጊዜን፥

እናስተውል ዛሬ ለኢትዮጵያችን የሚሻላትን፤

ለሁላችንም የሚበጀንን።

 

የሶዶቅ ምክር

 

ካህኑ ሶዶቅ እና ነቢዩ ናታን ሰሎሞንን ቀብተው እንዳነገሡት፤

ለቀዳማዊ ሚኒሊክም (የማክዳና የሰሎሞን ልጅ) እንዲሁ ተደረገለት።

ያኔ (ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት)፥

እንዲህ እያለ ነበረ ሶዶቅ ለቀዳማዊ ሚኒሊክ በየቀኑ የሚመክረው2፦-

“ልጄ ሆይ፦

ኑሮህ በእግዚአብሔር እምነት የፀና ይሁን፤

ሥራህ ሁሉ ስኬታማ እንዲሆን።

አንተ ጥሩ ስትሆን፥ ሕዝቡም አንተን ተከትሎ ጥሩ ይሆናል፤

ባንተ ሳቢያ ሕዝቡም አገሩም ይባረካል።

ድሆችን ከሚጨቁኗቸው - ከግፈኞች ነፃ አውጣቸው፤

በቀናውም መንገድ ምራቸው፤

በእኩልነት ተመልከታቸው።

ዳኝነትህም አድሎኣዊ እንዳይሆን ተጠንቀቅ፤

በሕግ ፊት - ማንም ከማንም እንዳይበልጥ እወቅ።”

ሁሉንም ለማግኘት 

ከዚህ ይጫኑ

According to 

3000 years ago, Priest Sodok, who annointed and crowned Minilik 1st, used to advise Minilik every day that his Kingdom (Ethiopia) will be blessed through him by God if he obeys God and be good.  

 

Read and enjoy the Poem.

  • Facebook App Icon
  • Twitter App Icon
  • Wix Google+ page

Copyright © 2018, M.H.Meskale, All rights reserved/ የኮፒ ራይት መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።

bottom of page