ሁሉም
ለኣንድነት
ከምድራዊነታችን ባሻገር
Beyond Our Earthly Realm
ጸረ ምድራዊ ስበት
ጸረ ምድራዊ ስበት
ልቦናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ
ልቦናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ
All
for Unity
እምነታችን-
"እውነት
ነጻነት
እኩልነት
ሕብረት
ጽድቅ
ሰላም
ፍቅር"
Our Belief-
"Truth
Freedom
Equality
Solidarity
RighteousnessPeace
Love"
"..እንደኛ አንድ
ይሆኑ ዘንድ
በስምህ
ጠብቃቸው።"
ዮሐ. 17፥11
"....protect them by the power of your name - the name you gave me - so that they may be one as we are one." John 17: 11
"This house is empty, but full of ideas".
Press the poems button to read Amharic poems
ግጥሞች ግጥምጥሞች
ሃሳብ ሲበራከት፥ ሲከብድ፥ ለመግለጽ ሲያስቸግር፥
ቋንቋም አልበቃ ሲል፥ በአፍ የሚነገር፥
ቢነገሩም፥ ተነግረው፥ ተነግረው ለማያልቁ ግትልትል ሃሳቦች፥
ጉራማይሌ ስሜቶች፥ “እንግዲህ በቃ!” የሚሉ፥ ስንኞች፥
“በቃ! ይኸው ነው ባጭሩ” የሚሉ፥ አጫጭር ቃሎች፥
የነገር መቋጥሮች፥ መተከዢያ ትዝታዎች፥
የሃሳብ ጭማቂዎች፥ የቅርቡን አጉሊዎች፥
የጥንቱን አስታዋሾች፥ ጊዜን ደምሳሾች፥ ፈጣን ባቡሮች፥
ቅዠትም ቢመስሉ፥ እውነታዎች፥
የሰማዩና የምድሩ ንኪኪዎች፥ ተስፋዎች፥ ልዩ መስተዋቶች፥
የእንባ ማድረቂያዎች፥ የናፍቆት አስታጋሾች፥
የፍቅር መግለጪያዎች፥ ማስተማሪያና ማወደሻ ቅኔዎች፥
መደሰቺያ ዘፈኖችና መዝሙሮች፥
መጸለያ ቅዳሴዎች።
ለእንቅስቃሴዎቻችን መንፈሳዊ ገጽታ ብንሰጣቸው!
If only our actions are connected to spiritual reflections !!
ሁሉም ከሁሉም ጋር ይያያዛል፤
ከሁሉም "በስተጀርባ" መንፈሳዊ ነጸብራቅ ይኖራል።
Everything is connected to everything, with spiritual reflections "behind"
አምላክ ሆይ! እባክህ አንተ የሚያቀራርበንን ጥበብ ለግሰን።