top of page

ሙሙዬ - ማማዬ

 

መግቢያ

 

እውቀት ሸመትን - ግንዛቤ ሸመትን.....

ክፉውንና ደጉን - ድንቁርናን እና ጥበብን ቀላቅለን፥

ከጦር ሜዳዎች እንዲሁም ከትምህርት ቤት ብዙ ብዙ ተማርን።

እውቀት ሸመትን - ግንዛቤ ሸመትን.....

የራሳችንን ለቀን - ይህንንም ያንንም - የባእዳኑንም ጨምረን፥

ከፖለቲከኞች ፖለቲካን ተማርን፤ ደጉንም ክፉውንም ወሰድን።

ሁሉን አግበስብሰን - ሁሉን መስለን፥

መለስ ስንል ወደራሳችን፥

የገዛ ታሪካችን አሳፈረን - በአሳሳች መነጽር እያየን፤

ከሌላውም ጋር በአንጻራዊነት እያወዳደርን፥

ራሳችንን መምሰል አቃተን - የኢትዮጵያዊነታችንን ጣእም ዘነጋን፤

መንፈሳዊ ባሕሬአችንን ለቀቅን፤

ማሕበራዊ ኑሮአችንን ትተን - ግለኞች ሆንን።

አዎ! በከንቱ የጥላቻ ፖለቲካ - በምድራዊ እውነታ - አይምሮአችንን አጣበብን።

እናም - ያወቅነውን፥ የሰማነውን፥ የተነገረንን፥ የተማርነውን ሆንን (መምሰል ብቻ ሳይሆን)።

ዛሬ - የገዛ ማንነታችን - የገዛ ዘራችን - መልሶ እኛን ጎዳን፤

የነገው ምን ይሆን? ምን ይሆን መጨረሻችን? ምን ይሆን መጨረሻችን።

ሁሉንም ለማግኘት 

ከዚህ ይጫኑ

አንድነት

"የሰው "እውቀቱ - እምነቱ" አንድ አደረገው? ወይንስ ለያየው? በሰውና በሰው መካከል ያለው ልዩነት እየተባባሰ የሄደው በሃብት ብቻ አይደለም፤ "በእውቀት - በእምነትም" ጭምር ነው እንጂ። በሃብት ከመበላለጥ የሚከፋው "በእውቀት - በእምነት" መበላለጥ ሳይሆን አይቀርም። ታዲያ እንዲህ በየአቅጣጫው እየሰፋ የሚሄደውን ልዩነት ለማጥበብ መፍትሄው እርስ በርስ በመግባባት አንድነታችን መሆን አለበት።"

Unity

 

"How can we narrow the gap between extreme ideas? And how can we narrow the gap between the so called the intelligentsia and the ordinary?

 

Let us undrstand one another and unite among ourselves and also with the Almighty God.." 

  • Facebook App Icon
  • Twitter App Icon
  • Wix Google+ page

Copyright © 2018, M.H.Meskale, All rights reserved/ የኮፒ ራይት መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።

bottom of page